Index   Back Top Print

[ AM  - AR  - BE  - BG  - CS  - DA  - DE  - EN  - ES  - FA  - FI  - FR  - HI  - HR  - HU  - HY  - IT  - JA  - KO  - LT  - LV  - ML  - NO  - PL  - PT  - RO  - RU  - SK  - SL  - SQ  - SV  - SW  - TA  - TI  - UK  - ZH ]

ለማርያም ንጹህ ልብ ራስን የመቀደስ ተግባር

 

ወላዲተ አምላክ እና እናታችን የሆንሽ ማርያም ሆይ እኛ በዚህ የመከራ ሰዓት ወደ አንቺ እንማጸናለን። አንቺ እናት ነሽ ትወጂናለሽ፣ እኛንም ታውቂናለሽ፤ ካንቺ የተሰወረ ምንም ነገር የለም። የምሕረት እናት ሆይ፣ ብዙ ጊዜ መለኮታዊ የሆነውን ርኅራኄሽን፣ በመካከላችን በመገኘትሽ ምክንያት ሰላምን ያስገኘበት ብዙ ጊዜያትን አግኝተናል፣ ስለዚህም ሁልጊዜ የሰላም አለቃ ወደ ሆነው ኢየሱስ እንድትመሪን እንጠይቅሻለን። 

እኛ ግን የሰላምን መንገድ አጥተናል። ባለፈው ክፍለ ዘመን የተከሰቱትን አሳዛኝ ሁኔታዎች፣ በዓለም ጦርነቶች ውስጥ የወደቁትን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መስዋዕት የሆኑ ሰዎችን ረስተናል። እንደ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የገባነውን ቃል ኪዳን ወደ ጎን በመተው የህዝቦችን የሰላም ህልም እና የወጣቶችን ተስፋ እየከዳን ነው። በስግብግብነት ታመናል፣ ራሳችንን በብሔራዊ ጥቅም ቆልፈን፣ በግዴለሽነት መንፈስ ሽባ እንድንሆን እና በራስ ወዳድነት ሽባ እንድንሆን ፈቅደናል። እግዚአብሔርን ቸል ማለት፣ ከውሸታችን ጋር መኖርን፣ ጠበኝነትን ማባባስ፣ ሕይወትን ማፈንና የጦር መሣሪያ ማሰባሰብን ወደድን፣ ለባልንጀራዎቻችን እና ለጋራ ቤታችን ጠባቂ መሆናችንን ረስተን ነበር። የምድርን ገነት በጦርነት አፈራርሰናል፣ ወንድሞችና እህቶች እንድንሆን የሚፈልገውን የአባታችንን ልብ በኃጢአት አቁስለነዋል። ከራሳችን በስተቀር ለሁሉም እና ለሁሉም ነገር ግድ የለሽ ሆነናል። እኛም በኀፍረት፡ - አቤቱ ይቅር በለን እንላለን። 

በኀጢአት መከራ፣ በውድቀታችንና በድክመታችን፣ ግልጽ በሆነው የክፋት እና የጦርነት ምስጢር፣ አንቺ ቅድስት እናታችን ሆይ፣ እግዚአብሔር እንደማይተወን ነገር ግን እኛን ይቅር ሊለን በሚጓጓ በፍቅር እንደሚመለከተን፣ እንደገና በይቅርታው ተነስተን እንጓዝ ዘንድ አስታውሽን።  አንቺን የሰጠን እና በንጹሕ ልብህ ውስጥ ለቤተ ክርስቲያን እና ለሰው ልጆች መጠጊያ እንድትሆኝ የሰጠን እርሱ ነው። በመለኮታዊ ቸርነት ከኛ ጋር ሁኚ እና በታሪክ ውስጥ ጠባብ በሆኑት ጊዜያት ሳይቀር በእርጋታ እንድንመላለስ እርጅን። 

እንግዲያውስ ለአንቺ መልስ እንስጥ፣ የልብሽን በር እናንኳኳ፣ አንቺ እኛ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት እንችል ዘንድ እኛን መጎብኘት መቸም ታክተሽ አታውቂም። በዚህ ጨለማ ሰዓት እኛን ለመርዳት እና ለማጽናናት ፍጥነሽ ነይ።  "እኔ እዚህ አይደለሁም ወይ፣ እናታችሁስ አይደለሁም ወይ?” የሚለውን ድምጽ ለእያንዳዳችን አሰሚን። የልባችንን እና የዘመናችንን ቋጠሮ እንዴት እንደሚፈታ አንቺ ታውቂያለሽ። በአንቺ ላይ እምነት አለን። በተለይ በችግሮቻችን ወቅት ልመናችንን እንደማትንቂ እና አንቺም እኛን እንደምትረጂን እርግጠኞች ነን። 

በቃና ዘገሊላ ባደረግሺው ተግባር ኢየሱስ ጣልቃ የሚገባበት ሰዓት እንዲፋጠን በማድረግ በዚህ ዓለም ውስጥ የእርሱ የመጀመሪያው ተዓምር እንዲፈጸም አድርገሻል። በዓሉ ወደ ኀዘን በተለወጠ ጊዜ፡— “የወይን ጠጅ የላቸውም” (ዮሐ 2፡3) በማለት ጣልቃ ገብተሻል። ይህንን ቃልሽን ዛሬም ለእግዚአብሔር ደግመሽ በይው፣ እናታችን ሆይ ዛሬ የተስፋ ወይን ጠጅ አልቆብናል፣ ደስታ ጠፋ፣ ወንድማማችነት ፈርሷል። ሰብአዊነትን አጥተናል፣ ሰላምን አጥተናል። ሁከትንና ጥፋትን ሁሉ ማድረግ ችለናል። በአስቸኳይ የናትነትሽን ጣልቃ ገብነት እንፈልጋለን። 

ስለዚህ እናታችን ሆይ ይህን ልመናችንን ተቀበይልን። 

አንቺ የባሕር ኮከብ ሆይ፣ በጦርነት ማዕበል ውስጥ ገብተን አንድንሰምጥ አትፍቀጂልን። 

አንቺ፣ የአዲስ ኪዳን ታቦት ሆይ፣ የእርቅ እና የሰላም መንገዶችን አነሳሺ። 

አንቺ፣ “የገነት ምድር ሆይ”፣ የእግዚአብሔርን ስምምነት ወደ ዓለም አምጪ። 

ጥላቻን አጥፊ፣ በቀልን አስወግጂ፣ ይቅርታ ማድረግን አስተምሪን። 

ከጦርነት ነፃ አውጥተሽን አለምን ከኒውክሌር ስጋት ነጻ እንዲሆን አድርጊ። 

የመቁጠሪያ ንግስት ሆይ የመፀለይን እና የመውደድን አስፈላጊነት በውስጣችን አንቂ። 

የሰው ልጆች ሁሉ ንግስት ሆይ ፣ ለሰዎች ሁሉ የወንድማማችነትን መንገድ አሳይ። 

የሰላም ንግሥት ፣ ለዓለም ሰላምን አስጪ። 

እናቴ ሆይ እንባሽ የደነደነ ልባችንን ያንጻው። ለእኛ ስትይ ያፈሰስሺው እንባ ይህ ጥላቻ ደርቆ የሚገኝበትን የልባችን ሸለቆ ያረስርስልን። የመሳሪያው ጩኸት ዝም ባይልም እንኳን የአንቺ ጸሎት ሰላምን ያጎናጽፈናል። የእናትነትሽ እጆች በቦምብ ጫና የሚሰቃዩትን እና የሚሸሹትን ሰዎች ሁሉ ይንከባከባሉ። የእናትነት እቅፍሽ ቤታቸውን እና አገራቸውን ጥለው ለመውጣት የተገደዱትን ያጽናናል። ያዘነው ልብሽ ወደ ርህራሄ እንዲወስደን እና በሩን እንድንከፍት እና የቆሰሉትን እና የተናቁትን የሰው ልጆች እንድንከባከብ ይገፋፋን። 

የእግዚአብሔር እናት የሆንሽ ቅድስት ሆይ ከመስቀል ሥር ሳለሽ ኢየሱስ ከጎንሽ ያለውን ደቀ መዝሙር አይቶ፡- “እነሆ ልጅሽ” (ዮሐ. 19፡26) ብሎ ነበር፣ ስለዚህም እያንዳንዳችንን ለእናንቺ አደራ ሰጠ። ከዚያም ለደቀ መዝሙሩ፣ ለእያንዳንዳችን፣ “እችሁና እናትህ” (ዮሐ 19፡ 27) አለ። እናታችን ሆይ አሁን ወደ ህይወታችን እና ታሪካችን እንኳን ደህና መጣሽ እንላለን። በዚህ ሰዓት የሰው ልጅ ደክሞ እና ተጨንቆ በመስቀል ስር ከእናንተ ጋር ይገኛል። በአንቺ በኩል ክርስቶስ ይቀድሰኝ ዘንድ ለአንቺ ራሴን በአደራ እሰጣለሁ። የዩክሬን ህዝብ እና የሩስያ ህዝቦች በፍቅር የሚያከብሩሽ፣ በጦርነት፤ በረሃብ፤ በፍትህ እጦት እና በመከራ ለተገደሉት ህዝቦች ሁሉ ምላሽ ትሰጪ ዘንድ ወደ አንቺ በፍጥነት ይመጣሉ። 

ስለዚህ የእግዚአብሔር እናት እና የእኛም እናት ይሆንሽ፣ እራሳችንን፣ ቤተክርስትያንን እና መላውን የሰው ዘር፣ በተለይም ሩሲያ እና ዩክሬን ንፁህ የሆነው የአንቺ ልብ ይቀድሳቸው ዘንድ በአደራ ወደ አንቺ አናቀርባለን። ጦርነቱ ይቆም ዘንድ እና አለም ሰላሙን ያገኝ ዘንድ፣  በፍቅር እና በመተማመን የምንፈጽመውን ተግባራችንን ተቀበይልን። ከልብሽ የወጣው “እንዳልከኝ ይሁንልኝ” የሚለው ቃል የታሪክን በሮች ለሰላም አለቃ  ልዑል የተከፈቱ ይሁኑ፣ በድጋሚ ንጹህ እና ቅዱስ በሆነው በአንቺ ልብ ሰላም እንደሚመጣ እናምናለን። ስለዚህ ለእናንቺ የመላው የሰው ልጅ የወደፊት እጣ ፈንታ፣ የሰዎች ፍላጎቶች እና ተስፋዎች፣ የአለምን ጭንቀት እና ተስፋዎች ትቀድሽ ዘንድ በፊትሽ እናቀርባለን። 

ባንቺ አማካኝነት መለኮታዊ ምህረት በምድር ላይ ይፈሳል እና የሰላም ጣፋጭ ምት ዘመናችንን ለማሳየት ይመለሳል። መንፈስ ቅዱስ የወረደባት “እንዳልከኝ ይሁንልኝ” ያለችው ሴት የእግዚአብሔርን አንድነት ወደ እኛ ትመልስልን፣ የልባችንን ድርቀት ያረካልን ዘንድ እናንተ "ሕያው የተስፋ ምንጭ ናችሁ" የሚለውን ድምጽ ለመስማት እንችል ዘንድ ትርዳን። የሰውን ልጅ ከኢየሱስ ጋር ሸምነህ፣ የኅብረት የእጅ ባለሞያዎች አድርጊን። በመንገዶቻችን ላይ የሄድሺው አንቺ፣ በሰላም ጎዳና ላይ እንድንራመድ እርጂን። አሜን። Copyright © Dicastero per la Comunicazione - Libreria Editrice Vaticana